ስለ አርኬ ዲጂታል
የአርኬ ምንነት እና ጥሪ
አርኬ ግሩፕ (Arke Group) በኢትዮጵያ ትምህርት እና ስብዕና ግንባታ ላይ አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የተነሳ የለውጥ ማዕከል ነው። "አርኬ" የሚለው ቃል ጥንታዊ የግዕዝ ትርጉሙ "ታማኝ ወዳጅ" ማለት ሲሆን፣ ተቋማችንም በትምህርት ማዕበል ለሚናወጠው ትውልድ እንደ "ኖኅ መርከብ" ሆኖ እውቀትን እና ስነ-ምግባርን ከአደጋ ለመታደግ ቆርጦ ተነስቷል።
መሠረታዊ እምነታችን
ዕውቀት ለስኬት፣ ሥነ-ምግባር ለሕይወት፤ አርኬ ለትውልድ!
ራዕይ 2035 (Vision 2035)
በ2035 በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ የልጆቻቸውን ስብዕና እና እውቀት ለመገንባት የሚያስችሉ የዲጂታል እና የአካል ትምህርቶች "ወርቃማው መለኪያ" (The Golden Standard) መሆን ራዕያችን ነው።
ተልዕኳችን (Mission)
🫳የቴክኖሎጂ ልቀት ፦ ዘመናዊ የጂፒኤስ (GPS) እና የዳታቤዝ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ብቁ መምህራንን በወላጆች እጅ ላይ ተደራሽ ማድረግ። 🫳የትውልድ ጥበቃ ፦ ለትውልዱ መበላሸት ምክንያት የሆኑትን ሱሶች እና መጥፎ ስነ-ምግባሮችን በእውቀት እና በምክር መዋጋት።🫳የዕድል ፈጣሪነት ፦ ለሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣት ምሁራን፣ ካህናት እና ዲያቆናት የላቀ ክብር እና አስተማማኝ ገቢ ያለው የስራ እድል መፍጠር።
የየኔታ አስጠኚ (የመንፈሳዊ ትምህርት)
ለልጆችዎ መንፈሳዊ እሴቶችን፣ ግዕዝ፣ ዜማ እና ስነ-ምግባርን በብቁ የኔታዎች በቤቶት ያስተምሩ። አሁን በመስራት ላይ ይገኛል።
የፊደል አስጠኚ (የአካዳሚክ ድጋፍ)
የክፍል ትምህርትን የሚያግዝ፣ ሂሳብ፣ ሳይንስ እና ቋንቋዎችን ያካተተ ዘመናዊ አካዳሚክ አስጠኚ። በቅርብ ቀን የሚጀመር።
የፊደል አስጠኚ የማንነት መሠረት